መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2014-በታሊባን አመራሮች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ መፈጠሩ ተሰማ

የታሊባን ቡድን መስራች ከሆኑት መካካል የሙላህ አብዱል ጋሃኒ ባራዳር እና የመንግስት ካቢኔ አባላት በካቡል ቤተመንግስት ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን ምንጮች አስታውቀዋል።ባለፉት ጥቂት ቀናቶችም ባራዳር ከህዝብ እይታ ተሰውረዋል።

የሃቃኒ ኔትወርክ አመራር በሆኑት የወቅቱ የስደተኞች ሚኒስትር ካሃሊል ራሃማን እና በባራዳር መካከል ጠንካራ የቃላት ልውውጥ እንደተፈጠረ ምንጮች ጠቁመዋል።በኳታር ዶካ የሚገኙ የታሊባን አባል ውዝግቡ ስለመፈጠሩ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

የውዝግቡ መነሻ ጊዜያዊው የአፍጋኒስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባራዳር በተዋቀረው አስተዳደር ደስተኛ አለመሆናቸው እንደሆነም ተነግሯል። በአፍጋኒስታን ለመጣው ድል ታሊባን የሚገባውን ያህል ክብር ሊያገኝ ይገባል በሚል ከሃቃኒ ኔትወርክ መስራቾች ጋር ልዩነቱ ሰፍቷል።

ለመጣው ድል የሃቃኒ ኔትወርክ የራሱ ድርሻ ያለው ሲሆን በቀድሞ የአፍጋኒስታን መንግስት ወታደሮችና በምዕራባውያን ሀይሎች ላክ ቡድኑ ጠንካራ ጥቃት ሲፈፅም ቆይቷል።አሜሪካ የሃቃኒ ኔትወርክን በአሸባሪነት ፈርጃለች።

የሃቃኒ ኔትወርክ መሪ ሲራጁዲን ሀቃኒ የአፍጋኒስታን አዲሱ መንግስት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ናቸው።አለመግባባቱን ተከትሎ ባራዳር ወደ ካንዳሃራ ከተማ ማምራታቸው ተሰምቷል።ባራዳር ግን ጉዟቸውን ለእረፍት የሚል ምክንያት ሰጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *