መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2014-አሜሪካ ለግብፅ የምታደርገዉን ወታደራዊ ዕርዳታ አቆመች

ግብፅ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ማሻሻያ እስክታደርግ ድረስ 130 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ወታደራዊ ዕርዳታን አሜሪካ አግዳለች፡፡የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸዉ ለግብጽ የሚደረገዉ መላዉ ዕርዳታ እንዲታገድ ጥሪ ቢያቀርቡም የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ግን 170 ሚሊዮን ዶላር ለካይሮ እንዲሰጥ አጽድቋል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከግብፅ ጋር በሰብዓዊ መብቶች ላይ መወያየቱን እንደሚቀጥል እና ግብፅ ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ካሟለች ቀሪውን ዕርዳታ እንደሚለቅ ይፋ አድርጓል፡፡የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን የአሜሪካ መንግስት የሰብአዊ መብቶችን ለማስፋፋት ያለውን ቁርጠኝነቱን አሳልፎ ሰጥቷል ሲሉ ከሰዋል።

በፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ አስተዳደር በርካታ የመብት ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የግብፅ መንግስት ግን በተደጋጋሚ የሚቀርብበትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ያስተባብላል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *