መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2014-የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር በፕሬዝዳንቱ ግድያ ተጠርጥረው ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

በወርሃ ሀምሌ ከተገደሉት የሄይቲ ፕሬዝዳንት ሞይሲ ጋር ተያይዞ የወቅቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪያል ሄነሪ ከሀገር እንዳይወጡ ታግደዋል። በፕሬዝዳንቱ ግድያ ዋንኛ ተጠርጣሪ ከተባለው ሰው ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነበራቸውን ግንኙነት እንዲያብራሩ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

በግድያው የተጠረጠረው ግለሰብ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆቭኔል ሞይሲ ከተገደሉ በኃላ በርካታ የስልክ ጥሪ በሁሉቱ መካከል እንደነበር አቃቢ ህግ አስረድቷል።በሞይሲ ግድያ ፖለስ 44 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ከነዚህ መካከል 18ቱ የቀድሞ የኮሎምቢያ ጦር አባላት ናቸው።

በተኙበት በ12 ጥይት ተደብድበው የተገደሉት የሄይቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ገዳዮች የአሜሪካና ኮሎምቢያ ዜግነት እንዳላቸው መነገሩ አይዘነጋም።ለአራት ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ሞይሲ በስልጣን ዘመናቸው ሀገሪቱን ለማረጋጋት ስድስት ጠቅላይ ሚኒስትሮችን መሾማቸው አይዘነጋም።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *