መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 7፤2014-የደቡብ ሱዳን ጳጳሳት በሀገሪቱ ሰላም ሂደት ተስፋ መቁረጣቸውን አስታወቁ

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የካቶሊክ ጳጳሳት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ግጭት ለማስቆም ከሦስት ዓመታት በፊት የተፈረመው የተሻሻለው የሰላም ስምምነት ሂደት በዝግታ መፈጸሙ እንዳበሳጨቸው ገልጸዋል። በጁባ ሊቀ ጳጳስ እስጢፋኖስ አመዩ ማርቲን በተፈረመው ደብዳቤ መሰረት ጳጳሳቱ የግጭቱ መንስኤዎች መፈታት አለባቸው ይላሉ።

የፖለቲካ መሪዎች ልባቸውን ቀይረው ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ ነፃነት እንዲሰጡ አሳስበዋል።በደቡብ ሱዳን ውስጥ ያለው የዜግነት ቦታ እየጠበበ መምጣቱ ያሳስበናል ያሉት ጳጳሳቱ ሁሉም ድምፆች እንዲሰሙ የፕሬስ ነፃነት ፣ ሀሳብን የመግለጽ ፣ የመናገር እና የመሰብሰብ ነፃነት እንዲከበር እንጠይቃለን ሲ.ሉ መልዕክቱ አስተላልፈዋል፡፡

ይህ መልዕክት የተላለፈዉ በኬንያና በደቡብ ሱዳን የቫቲካን አምባሳደር ሊቀ ጳጳስ በርት ቫን በተገኙበት የዉይይት መድረክ ነዉ፡፡ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የቀድሞው ተቀናቃኛቸው የወቅቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ፣ ከ18 ወራት በፊት የአንድነት መንግስት ቢመሰርቱም ፣ የ2018 የሰላም ስምምነት ቁልፍ አካል የሆነ የተዋሃደ ብሄራዊ ጦር ግን ገና አልመመስረታቸዉ የሰላም ሂደቱን አዝጋሚ አድርጎታል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *