መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 13፣2014- የሱዳን ጦር ጄነራል ሞሃመድ ሀምዳን ዳጎሎ ለተቃጣው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ፖለቲከኞችን ተጠያቂ አድርገዋል❗️

የሱዳን ገዢ ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የማክሰኞውን ያልተሳካ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠያቂዎች ፖለቲከኞች ናቸው ብለዋል።ሄሜቲ እየተባሉ የሚጠሩት ጄኔራል ዳጎሎ ከመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ ጀርባ ፖለቲከኞች አሉበት ምክንያቱም ዜጎችን ችላ ብለው በስልጣን ላይ እንዴት መቆየት እንዳለባቸው በመጨነቅ ላይ በመሆናቸው ነው ብለዋል።

ይህም በዜጎች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል ሲሉ ተናግረዋል።የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ በበኩላቸው ካልተሳካው መፈንቅለ መንግስት ጀርባ ከቀድሞ ስርዓት የተረፉ ሀይሎች ሴራ ማለታቸው ይታወሳል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ማሪያ አል ሳዲቅ አል ማህዲ እንደተናገረችው በወታደራዊ ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ የጦር መኮንኖች የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን የገቱ ሲሆን ይህም ለሀገሪቱ ሽግግር ያላቸውን ቁርጠኝነት ምልክት ነው ብለዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *