መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 19፤2014-ሰሜን ኮርያ በትላንትናው እለት ያስወነጨፍኩት ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ነው ስትል አስታወቀች

በትላንትናው እለት ሰሜን ኮርያ በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ያበለፀገችውን የሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል አስወንጭፋለች።በዛሬው እለት የሰሜን ኮርያ የዜና ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ሀገሪቱ በጦር አቅም ግንባታ የደረሰችበትን ደረጃ ሙከራው አመላክቷል ብሏል።

ሙከራው ሲደረግ በስፍራው የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ አን እንዳልነበሩ የተነገረ ሲሆን ፓክ ጆንግ ቾን የተባሉት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን በስፍራው ነበሩ።ሰሜን ኮርያ በተያዘው ወር እንዲህ አይነቱ ሙከራ ስታደርግ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

ይህ ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል ከተለመዱት ሚሳኤሎች ይልቅ እጅግ ፈጣን እና ቀልጣፋ እንዲሁም የመከላከያ ሥርዓቶቻቸውን ለመጥለፍ ከባድ ናቸው።የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በጥር ወር በነበረ ስብሰባ የሀገሪቱ ሳይንቲስቶች ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤልን እውን ለማድረግ ምርምር አጠናቀዋል ማለታቸው አይዘነጋም።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰሜን ኮርያ አምባሳደር ኪም ሶንግ በኒውዮርክ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ሀገራቸው ሰላሟን ለማስጠበቅ የብሄራዊ መከላከያ ግንባታን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *