መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 19፤2014-የአለም የጤና ድርጅት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊን ኮንጎ ሰራተኞች የወሲብ ጥቃቶች መፈፀማቸው ድርጅቱን ማስደንገጡ ተሰማ

የዓለም ጤና ድርጅት ያቋቋመው ገለልተኛ የምርመራ ቡድን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝን በመከላከል በነበሩ ሰራተኞች ከ80 በላይ የወሲብ ጥቃቶች እንደተፈፀሙ ተገልጿል።ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ 20 የአለም የጤና ድርጅት ሰራተኞች አሉበት ተብሏል።

በአገዳጅ መጠጥ እንዲጠጡ የተደረጉ ሴቶች በሆስፒታል ውስጥ በተፈፀመባቸው የአስገድዶ መደፈር ወንጀል መፀነሳቸው ተስምቷል።የአለም የጤና ድርጅት የቀጠናው ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞኢቲ እ.ኤ.አ ከ2018 እስከ 2020 ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ ተናግረዋል።

ከተጎጂዎች ጎን በመሆን ፍትህ እንዲሰጥ ለማድረግ እንሰራለን ሲሉ የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *