
ከሰሜን ወሎ ሀራ ወረዳ ተፈናቅለው በኮምቦልቻ የሰፈሩ ተፈናቃዮች ቁጥር 321 መድረሱ ተነግሯል ።
ከተፈናቃዮቹ ውስጥ 8 የሚሆኑት እናቶች በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የወለዱ ሲሆን በአሁን ሰራት 6 ለመውለድ የደረሱ እናቶች ናቸው ብስራት ሬድዮ በስፍራው ተገኝቶ እንደተመለከተው ከእነዚህ እናቶች በተጨማሪ 41 የሚሆኑት የሚያጠቡ እናቶች ናቸው ።
የተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝም ተናግሯል ።ተፈናቃዮቹ ከሁለት ወር በላይ በመጠለያ ውስጥ አስቆጥረዋል ።
የቢጂ አይ ኢትዮጲይ ኮምቦልቻ ፋብሪካ እነዚህኑ ፣በኮምቦልቻ ፣ ደሴ ከተማዋ እና ዙሪያዋ ለሰፈሩ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል።
ናትናኤል ሀብታሙ