መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 20፤2014-አንድ ግድብ አይደለም ለልማት አስፈላጊ ከሆነ ሌላም እንጨምራለን ሲሉ አምባሳደር ዲና ተናገሩ❗️

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬዉ እለት ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫውም ከተነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ የታላቁን የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብን የተመለከተ ነዉ፡፡

ካስፈለገ አንድ ግድብ ሳይሆን ለልማት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኙ ሌላ መገንባታችን አይቀርም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መናገራቸዉን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል፡፡ በቱኒዚያ በኩል እየተባለ ያለው ይህንን ውሃ አንጠቅምም ብላችሁ ፈርሙ የሚልዉን ኢትዮጵያ አትፈርምም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ግድብ አንዴ ጀምራቹኃል ጨርሱ ሆኖም ግን ከዚህ ግድብ ውጪ ሌላ መስራትም ሆነ የመጠቀም መብት አይኑራችሁ የሚል ፊርማ ነው የቀረበው ኢትዮጵያ ግን እንደዚህ አይነት ስምምነት ውስጥ አትገባም የቀረበላትንም አትፈርምም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

በቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *