
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደው ባለው 6ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ የምስረታ ጉባኤው ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታን አፈጉባኤ አድርጎ መርጧል።
ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ፣ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ ፣ የጋህአዴን ጽህፈት ቤት ሃላፊ እንዲሁም ከአንድ አመት በፊት በተደረገው ሽግሽግ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ሆነው ያገለገሉ ናቸው።
አፈ ጉባኤዋ ለህገ መንግሥቱ ታማኝ በመሆን ከክልሉ እና ከህዝቡ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በቅንነትና በታታሪነት እንዲሁም ህግና ስርአትን መሠረት በማድረግ ስራቸውን እንደሚፈጽሙ ቃል ገብተዋል።
በሚኪያስ ፀጋዬ