መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 24፤2014-የዓለም መሪዎች እና ቢሊየነሮች ምስጢራዊ የሀብት ግንኙነትን የያዘ ሰነድ ይፋ ሆነ

ፓንዶራ በተሰኘው ሰነድ ውስጥ የወቅቱ እና የቀድሞ 35 የሀገራት መሪዎች እና ከ300 በላይ የመንግስት ባለስልጣናት ይፋ ሆኗል።በሰነዱ ይፋ ከሆኑት መካከል የዮርዳኖስ ንጉስ በድብቅ በእንግሊዝ እና አሜሪካ 70 ሚሊዮን ፓውንድ የሚሆን ንብረት ማከማቸታቸውን ይህው ምስጢራዊ ሰነድ አጋልጧል።

የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ ሁለተኛ ቢን አል ሁስኒ እ.ኤ.አ በ1999 በስልጣን ላይ ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ 15 ቤቶችን ገዝተዋል።በማሊቡ፣ለንደን እና አስኮ መኖሪያ ቤቶች አሏቸው።

የእንግሊዝ የቀድሞ ጠ/ሚ ቶኒ ብሌየር እና ባለቤታቸው በለንደን የቢሮ ጽህፈት ቤት ሲገዙ እንዴት 312ሺ ፓውንድ ቀረጥ ሳይከፍሉ መግዛታቸውን አጋልጧል።ጥንዶቹ ከአንድ ኩባንያ ይህንኑ ፅህፈት ቤት ገዝተዋል።

በምስጢራዊው ሰነድ ውስጥ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሞናኮ ሀብት ማከማቸታቸውን እንዲሁም የቼክ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሬጅ ባቢስ በደቡባዊ ፈረንሳይ በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ሁለት የመኖሪያ ቪላዎችን ለመግዛት ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱ ይህ ሰነድ አጋልጧል።

ባለፉት ሰባት አመታት በተከታታይ የፊንኬን ሰነዶች፣የፓራዳይዝ፣የፓናማ እና ሉክሌክስ የተሰኙ ሚስጢራዊ ወረቀቶች ይፋ ሆነዋል።የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራሃን ካሃን፣የኬንያው ኧሁሩ ኬንያታ በፓንዶራ ሰነድ ምስጢራዊ የሀብት መጠናቸው ይፋ ተደርጎባቸዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *