መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 27፤2014-በፓኪስታን በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

በፓኪስታን በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

በትላንትናው እለት በፓኪስታን ባሎቺስታን ግዛት በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያንስ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።የመንግስት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በአደጋው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልፀዋል።

ከሟቾቹ አብላጫውን ቁጥር የያዙት ሴቶችና ህፃናት እንደሆኑ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል።የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂ ጥናት መሰረት የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.9 የተለካ እንደሆነም ገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ 150 ያህል ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል።ከ100 በላይ መኖሪያ ቤቶችም በአደጋው ክፉኛ ወድመዋል።የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የነፍስ አድን ርብርብ እያደረጉ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *