መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 28፤2014-በአፍጋኒስታን በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት የሟቾቹ ቁጥር 55 ደረሰ

በአፍጋኒስታን ኩንዱዙ ከተማ በአንድ መስጊድ ውስጥ በዛሬው እለት በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ 55 ሰዎች መገደላቸውን የመንግስት ባለስልጣናት አስታውቋል።የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው ደም አፍሳሽ ጥቃት ሆኖ ተመዝግቧል።

በጥቃቱ ህይወታቸውን ካጡት ሰዎች በተጨማሪ ከ100 በላይ ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል።ለጥቃቱ እስካሁን ድረስ ሀላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በሺያ ማህበረሰብ ላይ ጥቃት በመፈጸም የሚታወቀው አይኤስ ጥቃቱን ሊፈፅም እንደሚችል ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ የዜና ወኪል የሆነው ቶሎ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ በፀሎት ስነ ስርዓት ላይ ከ300 በላይ ሰዎች ሰኢድ አባድ በተባለው መስጊድ ውስጥ እንደነበሩ ተመልክቷል።የኩንዱዙ ከተማ ነዋሪዎች የነፍስ አድን ስራው የተፋጠነ እንዲሆን የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *