መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 28፤2014-ኢትዮጵያን ጨምሮ 47 የአለም ሀገራት ከእንግሊዝ የጉዞ ቀይ መዝገብ ዝርዝር ውስጥ ነጻ ሆኑ

በእንግሊዝ የኮቪድ 19 የጉዞ ቀይ ዝርዝር ውስጥ ካሉ 54 አገራት ቁጥር ወደ ሰባት እንዲቀንስ መደረጉን የሀገሪቱ መንግስት አስታዉቋል፡፡ከዝርዝር ዉስጥ ከወጡት መካከል ደቡብ አፍሪካ ፣ ብራዚል እና ሜክሲኮ ተጠቃሽ ሲሆኑ ፣ ይህም ተጓዦች በተፈቀደላቸው ሆቴል ውስጥ ለ10 ቀናት ራሳቸዉን እንዲያገሉ የሚያስገድደዉን ህግ ያስቀራል፡፡

የትራንስፖርት ዋና ፀሐፊ ግራንት ሻፕስ ማሻሻዉ ሰኞ የሚጀምር ሲሆን ጉዞን በመክፈት ቀጣዩ እርምጃ ለመመልከት ያስችላል ብለዋል፡፡ይህ ዉሳኔ በወረርሽኙ ምክንያት መገናኘት ያልቻሉ ቤተሰቦችን በድጋሚ እንዲገናኙ እና ለአየር መንገድ ኢንዱስትሪ መነቃቃትም ትልቅ አስተዋጾ እንዳለዉ ተጠቁሟል፡፡

ሁሉም መንገደኞች ግን የተሳፋሪ አመልካች ቅጽን የመሙላት ግዴታ አለባቸዉ። አሁንም ፓናማ ፣ ኮሎምቢያ ፣ ቬኔዝዌላ ፣ ፔሩ ፣ ኢኳዶር ፣ ሄይቲ እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ በኮቪድ 19 የእንግሊዝ የጉዞ ቀይ ዝርዝር ውስጥ እንዲቆዩ ያስገድዳቸዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *