መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 28፤2014-ጋዜጠኞቹ ማሪያ ሬሳ እና ሙራቶቭ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸነፉ

ጋዜጠኞቹ ማሪያ ሬሳ እና ድሚትሪ ሙራቶቭ በፊሊፒንስ እና በሩሲያ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ደፋር ትግል ማድረጋቸዉን ተከትሎ የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል።የኖቤል ኮሚቴው ጋዜጠኞቹ ዴሞክራሲ እና የፕሬስ ነፃነት ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት በዚህ ዓለም ለሙያቸዉ የቆሙ የሁሉም ጋዜጠኞች ተወካይ ናቸዉ ሲል ጠርቷቸዋል።

ሽልማት አሸናፊዎቹ በኦስሎ ከሚገኘው የኖቤል ተቋም ይፋ እንደሆነዉ 10 ሚሊዮን የስዊድን ክሮና ወይም 1.1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያገኛሉ፡፡ከ 329 ዕጩዎች ውስጥ በመመረጥ አሸናፊ ለመሆን በቅተዋል፡፡

በዚህ ዓመት በተፎካካሪነት ተጠቆመዉ ከቀረቡት መካከል የአየር ንብረት ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ ፣ የመገናኛ ብዙኃን መብት ተከራካሪ የሆነዉ ድንበር አያግዴዉ የዘጋቢዎች ቡድን እና የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በእጩነት ቀርበዉ ነበር፡፡ረሃብን ለመዋጋት እና ለሰላም ሁኔታዎች መማሻሻል ባደረገው ጥረት የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ባለፈው ዓመት አሸናፊ የነበረ ሲሆን በ2019 ደግሞ የኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሸናፊ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *