
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 6 ሺህ 163 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ ነው።
ከተመራቂዎቹ መካከል 155 የሶስተኛ ዲግሪ ዕጩ ምሩቃን ናቸው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ከተመራቂዎቹ መካከል 2 ሺህ 559 ድሕረ ምረቃ፣ 3 ሺህ 604 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ ፥ 1 ሺህ 883ቱ ሴቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።