መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 29፤2014-የኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ድርጅት በ2013 በጀት ዓመት 86 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ❗️

የኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ድርጅት በ2013 በጀት ዓመት 86 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ❗️

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በየአመቱ የሚከበረውን የአለም ፖስታ ቀንን ምንክንያት በማድረግ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሀና አርአያ ስላሴ በ2013 በጀት አመት 86 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።ይህም ከእቅዱ 111 በመቶ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ድርጅቱ አሰራሩን ለማዘመን የተለያዩ ተግባራቶችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህም ዉስጥ የተለያዩ ተጨማሪ ቅርጫፎችን በመክፈት እንዲሁም ሁሉንም ቅርንጫፎች በኔትወርክ የማስተሳሰር ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

ድርጅቱ የኮቪድ 19 ናሙናዎችን ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ወደ ዉጪ የማመላለስ ስራንም ሲሰራ እንደቆየ አስታውቀዋል።ድርጅቱ ለውጡን ለማፋጠን በአዲስ ፈጠራ በአዲስ ምዕራፍ እንደሚንቀሳቀስ አስታውቋል።

በተያዘው በጀት አመትም አሰራሮችን በማዘመን የፖስታ መልእክቶችን ደህንነት እና ፍጥነት ላይ የተገልጋዩን ፍላጎት ለማርካት እንደሚሰራ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።በዛሬው እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖስታ ቀን እየተከበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ቀደምት የቴምብር ህትመቶችን ለእይታ አብቅቷል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *