መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 1፣2014-በወራቤ ከተማ የተቀቀሰው እሳት ከአንዲት ግለሰብ የቤንዚል ችርቻሮ መሽጫ ሱቅ የተነሳ መሆኑ ተነግሯል።

updated

በወራቤ ከተማ የተቀቀሰው እሳት ከአንዲት ግለሰብ የቤንዚል ችርቻሮ መሽጫ ሱቅ የተነሳ መሆኑ ተነግሯል።

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 2 በሚገኘው የቤንዚል መሸጫ ሱቅ ውስጥ የተነሳው እሳት በሱቁ ውስጥ የነበረች ግለሰብ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት በማድረስ በህክምና ድጋፍ ላይ ትገኛለች ተብሏል።

በእሳት አደጋው 40 ሺ ብር ጥሬ ገንዘብ የተቃጠለ ሲሆን በአጠቃላይ አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ስልሳ ሺ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር በህረዲን ሀሰን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በከተማው የእሳት አደጋ ተሽከርካሪና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ የእሳት አደጋው በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል።

የእሳት አደጋው ከዚህም በተጨማሪ ለአራት የላሜራ ቤቶች መቃጠል ምክንያት መሆኑን ኮማንደር በህረዲን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *