መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 1፤2014-በኦሃዮ አንድን ጥቁር አካሌ መታዘዝ አይችልም እያለ ከመኪናዉ በማስወረድ መሬት ለመሬት በፖሊስ መጎተቱ ቁጣ አስነሳ

የዩናይትድ ስቴትስ ፖሊስ አንድ ጥቁር ሰው ሰዉነቴ አይታዘዝልኝም እያለ በተደጋጋሚ ቢጮህም ከመኪና ሲጎትት የሚያሳይ ቪዲዮ መጋራቱን ተከትሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታዉቋል፡፡የቪዲዮ ምስሎቹ እንዳሳዩት የፖሊስ መኮንኖች ባለፈው ወር በኦሃዮ ውስጥ ኦዌንስቢ የተባለዉን ግለሰብ በማስቆም የአደንዛዥ ዕፅ ፍተሸ ለማድረግ ከመኪናው እንዲወጣ ሲጠይቁት ያሳያል።

የ39 ዓመቱ ኦዌንስቢ እግሮቼን መጠቀም አልችለም ለዚህም መዉረድ እንደሚከብደዉ ሲናገር ይታያል፡፡ኦዌንስቢ ለእርዳታ የስልክ ጥሪ እያደረገ ባለበት የፖሊስ መኮንኖቹ ከተሽከርካሪው ፀጉሩ እና እጆቹን በመጎተት ሲያስወርዱት ተስተዉሏል፡፡

የአካባቢዉ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የፖሊስ መኮንኖቹ ኦዌንስቢን ያቆሙት በአደንዛዥ ዕፅ ተሳትፎ ከተጠረጠረ ቤት ተሸከርካሪን አስነስቶ እየነዳ ሲወጣ ከተመለከቱት በኃላ ነዉ፡፡ ፖሊስ በመኪናው ውስጥ 22,450 ዶላር የያዘ ቦርሳ አግኝቻለሁ ብሏል።

የዴይተን ፖሊስ መምሪያ ድርጊቱ ከ12 ቀናት በፊት መፈጸሙን በመግለጽ ምርመራ እያደረገ ስለመሆኑ ገልጿል፡፡ኦዌንስቢ በማንኛውም ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዙ ጥፋቶች ከዚህ ቀደም ተከሶ አያዉቅም፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመባት የኦሃዮ ዴይተን ከተማ ከንቲባ ናን ዌሊ በቀረፃው የተመለከትኩት ነገር በጣም አሳሳቢ በማለት ገልፀዉታል።የሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ድርጊቱን እያጣር ነዉ ብለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *