መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2014-በደቡብ ክልል በ2014 በጀት ዓመት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ120 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ክልል በ2014 በጀት ዓመት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ120 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ክልል የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በ15 ዞኖች እና በ7 ልዩ ወረዳዎች 264 አደጋዎች መከሰታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ አደጋ መከላከል ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት መረጃ እና ስታክቲክስ ዲቪዝን ተወካይ ምክትል ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ከሀምሌ 1 እስከ መስከረም 30 በተከሰተው አደጋ 121 ሞት፣108 ከባድ የአካል ጉዳት እና 4 ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።እንዲሁ በገንዘብ ሲተመን ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ወድሟል።

ከደረሰው አደጋ ከፍተኛ የጉዳት መጠን የተመዘገበው በደቡብ ኦሞ፣በሀድያ፣በጌድዮ፣በቤንችሸኮ እና በከንባታ ጠንባሮ ዞኖች የደረሱ ናቸው፡፡

በብዛት በትራፊክ አደጋው ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች የእድሜ ክልል ከ18 እስከ 30 ነው ተብሏል።

ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት እና የአሸከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት የአደጋው መንስኤዎች ናቸው ሲሉ ኢንስፔክተር ታምራት ደሳለኝ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *