መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2014-በአይፎን 13 ምርት ፍራቻ የአፕል የአክሲዮን ድርሻ ቀነሰ

በአይፎን 13 ምርት ፍራቻ የአፕል የአክሲዮን ድርሻ ቀነሰ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮምፒተር ቺፕ እጥረት በመከሰቱ የተነሳ የአፕል አክሲዮኖች በትላንትናዉ እለት ወርዷል፡፡ግዝፉ የኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ በ2021 የመጨረሻ ሩብ ዓመት ውስጥ 90 ሚሊዮን አይፎኖችን ይሠራል ተብሎ ይጠበቅ እንደነበር ብሉምበርግ ዘግቧል።

ሆኖም ግን አፕል አሁን ላይ በ10 ሚሊዮን አስቀድሞ ካቀደዉ የቀነሰ እንደሚያመርት የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል።ይህ መረጃ ይፋ ከተደረገ በኃላ የአፕል አክሲዮኖች 1.2 በመቶኛ ቀንሷል።

የሴሚኮንዳክተር አምራቾቹ ብሮድኮም እና ቴክሳስ እንዲሁ 1% የአክሲዮን ድርሻቸዉ ቀንሷል ፣ ምንጮች እንደሚሉት ተቋማቱ በቂ ቺፕስ ለአፕል በወቅቱ ለማቅረብ እየታገሉ እንደነበሩ ተናግረዋል።

በመስከረም ወር አፕል አራት አዳዲስ የአይፎን 13 ሞዴሎችን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ አይፎን 13 ፣ አይፎን 13 ሚኒ ፣ አይፎን 13 ፕሮ እና iPhone አይፎን 13 Pro ማክስ ቅድመ-ትዕዛዞች ከመስከረም 17 ጀምሮ ኩባንያዉ ሲቀበል ነበር፡፡በበርካታ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምርቶች በኮምፒተር ቺፕስ እጥረት ችግር ዉስጥ ናቸዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *