መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2014-ባለፉስ ሶስት ወራት በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል❗️

ባለፉስ ሶስት ወራት በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል❗️

በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ባለፉት ሶስት ወራት በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የ32 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሀያ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል፡፡

በእሳት አደጋ ሶስት ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጣ 29 ሰዎች ደግሞ በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተነግራል፡፡

በነዚህ አደጋዎች ከሀያ ሁለት ሚሊየን ስድስት መቶ ሺ በላይ የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን ከአንድ ቢሊየን 38 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረትን ከውድመት ማትረፍ መቻሉን ኮሚሽኑ አስታውቃል፡፡

በ2014 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞኖች አንድ መቶ አስራ አራት ድንገተኛ አደጋዎች መድረሳቸውን የኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።106 አደጋዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ ሲሆን ቀሪ ስምንት አደጋዎች በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደረሱ ናቸው፡፡

ከአደጋዎች መካከል 58ቱ የእሳት አደጋ ሲሆን 56 ያህሉ ደግሞ ድንገተኛ አደጋዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ አሳይቷል። በሞት መጠን ባለፈው ዓመት 23 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በዘንድሮ ሩብ ዓመት በዘጠኝ ጨምሮ 32 ሰዎች ህይታቸውን አጥተዋል።

ከደረሱት 64 አደጋዎች መንስኤቸው የታወቀ ሲሆን ቀሪ 50 ያህል አደጋዎች ምክንያታቸው አለመታወቁን አቶ ጉልላት ጌታነህ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *