መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 9፤2014-ቡሩንዲ የአፍሪካ የመጨረሻዋ ሀገር በመሆን የኮሮና ክትባት መስጠት ጀመረች

ቡሩንዲ የአፍሪካ የመጨረሻዋ ሀገር በመሆን የኮሮና ክትባት መስጠት ጀመረች

ቡሩንዲ ዜጎቿን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠት መጀመሯን በይፋ ገልጻለች፡፡ከትባቱን ዘግይታ መስጠት የጀመረችዉ ቡሩንዱ በአፍሪካ ብሎም በዓለም ላይ ካሉት ዘግይተዉ ክትባት መስጠት የጀመሩ ሀገራት ተርታ ትገኛለች፡፡

ክትባቱ ፍቃደኝነት ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን በቡጁምቡራ ከተማ ዉስጥ ለመከተብ ያለዉ ፍላጎት በአንፃራዊነት ዝቅተኛ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡እስካሁን ድረስ ሰዎች ክትባት ለመዉሰድ እንዲመጡ ለማበረታታት በመንግስት በኩል የተደረገ ሙከራ የለም።

ባለፈው ሳምንት ቡሩንዲ 500,000 የሲኖፋርም ክትባት ተረክባለች፡፡በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስትሩ ታድዬ ንዲኩማና ለጤና ሰራተኞች እና አረጋውያን ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ባለፈው ሳምንት እንደተናገሩት ቡሩንዲ ፣ ኤርትራ እና ሰሜን ኮሪያ የኮቪድ ክትባት ያልጀመሩ ብቸኛ የአለም ሀገራት ናቸው ሲሉ መናገራቸዉ አይዘነጋም።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *