መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፤2014-ሴኔጋል ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር አዋለች

ሴኔጋል ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር አዋለች

በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ሴኔጋል በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን የተሰኘ አደንዛዥ እፅ መያዙን ሮይተርስ የዜና ወኪሉ የባህር ኃይል መግለጫን ጠቅሶ ዘግቧል። ከፈረንሣይ አየር ኃይል ጋር በመጣመር በተደረገው ዘመቻ 2,026 ኪሎ ግራም ኮኬይን በሴኔጋል ባህር ጠረፍ በአንድ በመርከብ ላይ መግኘቱን መግለጫው አመልክቷል።

ከሴኔጋል የባሕር ጠረፍ በ363 ኪሜ ርቀት የተገኘችው መርከብ አምስት የመርከብ ሠራተኞች እንደነበሩባት ታውቋል።የምዕራብ አፍሪካ ቀጠና በደቡብ አሜሪካ እና በአውሮፓ መካከል የአደንዛዥ ዕፅን ለማዘዋወር የመተላለፊያ መስመር እየሆነ ይገኛል።

በጥር ወር የሴኔጋል ጎረቤት ጋምቢያ በኢኳዶር የተመረተ የኢንዱስትሪ ጨው ጭነት ውስጥ ሦስት ቶን የሚጠጋ ኮኬይን በቁጥጥር ስር ማዋሏ አይዘነጋም።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *