መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፤2014-በሶርያ መዲና ደማስቆ በወታደራዊ አዉቶቢስ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ ቢያንስ 14 ሰዎች ተገደሉ

በሶርያ መዲና ደማስቆ በወታደራዊ አዉቶቢስ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ ቢያንስ 14 ሰዎች ተገደሉ

በማዕከላዊ ደማስቆ በወታደራዊ አውቶቡስ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሶሪያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።በተሽከርካሪው ላይ የተጠመዱ ሁለት ፈንጂ መሣሪያዎች ዛሬ ማለዳ ሰዓት ጅስር አል ራይስ በተሰኘ ድልድይ ስር ሲያልፍ ፍንዳታዉ መከሰቱን ሳና የዜና ወኪል ዘግቧልለለ

ሶሪያ ከአስር ዓመታት በላይ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ብትገኝም በመዲናዋ እንደዚህ ዓይነቱ ጥቃት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ይህ መረጃ በተሰማ በጥቂት ሰዓታት ልዩነት በተቃዋሚዎች እጅ ስር በሚገኘዉ ሰሜን ምዕራባዊ ሶርያ ውስጥ አማጺያን ከሠራዊቱ ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ 10 ሰዎች ተገድለዋል፡፡

የፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድን አስተዳደርን ለመጣል ሲሞክሩ የቆዩ አማጺያን እና የጂሃዲስት ቡድኖች የመጨረሻ ምሽግ ሰሜን ምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ነዉ፡፡የጸደዩን የአረብ አብዮት ተከትሎ የተቀሰቀሰዉ የሶርያ ጦርነቱ ቢያንስ የ350,000 ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በሀገር ዉስጥ ስድስት ሚሊዮን ያህል ሶርያዉያንን ደግሞ ሀገር ለቀዉ እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል፡፡

በዛሬዉ እለት በደማስቆ የተፈጸመው ጥቃት በሀገሪቱ ዋናዉ ፍርድ ቤት በ2017 አይ ኤስ 31 ሰዎች ከገደለበት ደም አፍሳሽ ጥቃት በኃላ ከፍተኛ በሚል ተመዝግቧል፡፡ለጥቃቱ እስካሁን ድረስ ሀላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም አይኤስ ሊፈጽመዉ እንደሚችል ግን ተገምቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *