መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 10፤2014-የአረብ ሀገራት ከበሽር አላ አሳድ ጋር ግንኙነት መመስረት መጀመራቸው አሜሪካ በሶርያ ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ ከቷታል

የአረብ ሀገራት ከበሽር አላ አሳድ ጋር ግንኙነት መመስረት መጀመራቸው አሜሪካ በሶርያ ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ ከቷታል

የቀጠናው የፖለቲካ ጥናቶች ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከሆነ የሶርያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከስልጣን ይወርዳሉ ተብሎ አይጠበቅም ብለዋል።ከበርካታ የአረብ ሀገራት ጋር ደማስቆ ግንኙነቷን እያጠናከረችም ትገኛለች።

ዋሽንግተን በሶርያ ላይ የምታራምደውን ፖሊሲ ሚዛናዊ አድርጎ ለማስቀጠል የደማስቆ መንግስት ከቀጠናው ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት መመስረታቸው ለአሜሪካ አጣብቂኝ አድርጎታል።በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ሞና ያኩቡኒን የባይደን አስተዳደር በሶርያ ዙሪያ እና በቀጠናው መሬት ላይ ያለውን ሀቅ መቀበል ይኖርበታል ብለዋል።

የፀደዩን የአረብ አብዮት ተከትሎ በ2011 የተቀሰቀሰው የሶርያ ጦርነት መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ ቢያስከትልም የደማስቆ መንግስት በእሳት እየተፈተነ ስልጣኑን ማጠናከር ችሏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *