መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 15፣2014-ጎህ ቤቶች ባንክ በይፋ ስራ ጀመረ

ጎህ ቤቶች ባንክ በይፋ ስራ ጀመረ

ጎህ ቤቶች ባንክ በትላንትነው እለት በይፋ ስራ መጀመሩን ለጋዜጠኞች በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቋል። ባንኩ የሚታየዉን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ አልሞ ለቤት ፈላጊዎች የተሟላ ብድር ለመስጠት እንዲሁም አቅሙን እያሳደገ ሲመጣ በባንኩ ካፒታል ቤቶችን እየገነባ ለተጠቃሚዎች እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል።

የባንኩ ስራ አስፈፃሚ ሙሉጌታ አስማረ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ባንኩ በመካከለኛ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላሉ ዜጎች የቤት አቅርቦቱን ለማሻሻል እንደሚሰራ ተናግረዋል። ባንኩ በብር 1.1 ቢሊዮን የተፈረመ ካፒታል እና በ 521.5 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል በ6 ሺህ 658 ባለአክሲዮኖች መመስረቱን ስራ አስፈፃሚዉ አስታውቀዋል ።

በከተማ ዉስጥ ለሚታየው የመኖሪያ ቤት እጥረት ሁነኛ መፍትሔን ይሰጣል ያሉት ስራ አስፈጻሚው ቤት ለመስራት እና ለመግዛት ለሚፈልጉ ዜጎች እስከ 30 ዓመት የሚዘልቅ የብድር ጊዜ አመቻችቷል ብለዋል ።በመሆኑም በተያዘው በጀት አመት እስከ 1.3 ቢሊዮን የሚጠጋ ቁጠባ ለመሰብሰብ እና 1 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠትም አቅዷል ።

ባንኩ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ቅርንጫፎችን በመክፈት የሚታየዉን የቤት እጥረት ለመቅረፍ አስተዋጽኦዉን እንደሚያደርግ አቶ ሙሉጌታ ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡

በረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *