መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 16፤2014-በአዲስ አበባ የግእዝ ቋንቋን የሚያስተምር ትምህርት ቤት ሊመሰረት ነዉ

በአዲስ አበባ የግእዝ ቋንቋን የሚያስተምር ትምህርት ቤት ሊመሰረት ነዉ

በአዲስ አበባ በተለምዶዉ ላምበረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለዉ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ግእዝ ቋንቋን የሚሰጥ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

የትምህርት ቤቱ መስራች አቶ ይባቤ አዳነ እንዳስታወቁት ትምህርት ቤቱ ግንባታዉን በሚቀጥለው አመት ተጠናቆ በ 2015 ዓ.ም መማር ማስተማር ሂደት ለመጀመር መታቀዱን ተናግረዋል።

የግእዝ ቋንቋ የኢትዮጵያውያን ቋንቋ መሆኑን አቶ ይባቤ ተናግረዉ ቋንቋው ዘርፈ ብዙ እዉቀቶችን አጭቆ የያዘ በመሆኑ በትምህርት ስርአት ዉስጥ ማስገባት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።

በመድረኩ በስነፅሁፍ እና በመምህርነት እዉቅናን ያተረፉት መምህር እና ፀሀፊ ሀይለመለኮት መዋእል እና መምህር ታዬ ቦጋለ እንደተናገሩት ግእዝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ብቻ ሳይሆን የመላዉ ኢትዮጵያውያን በመሆኑ ሁሉም በዉስጡ ያለዉን እምቅ እዉቀት ሊመረምረዉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ 53 ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ የሚገነባ ሲሆን ከመዋለ ህጻናት እስከ መሰናዶ የሚያካትት መሆኑን ፕሮጀክቱን ያዘጋጁት አርክቴክት ኤፍሬም ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *