መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 16፤2014-ባትማን የተባለ ስናክስ ምርትን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ጥሪ ቀረበ❗️

የመጠቀሚያ ጊዜ የሌላቸው ብስኩቶችና ምንነታቸው የማይታወቁ ማጣፈጫዎችን በመጠቀም ባትማን የተባለ ስናክስ እና ንጽህና በጎደለው ቦታ የምግብ ዘይት ሲያመርቱ የተገኙ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ እና ከቡራዩ፣ ሱሉልታ ፖሊስ ጋር በቅንጅት በመሆን ጥቅምት 13 ቀን በተወሰደ እርምጃ የመጠቀሚያ ጊዜ የሌላቸው ብስኩቶችና ምንነታቸው የማይታወቁ ማጣፈጫዎችን በመጠቀም ባትማን የተባለ ስናክስ በቡራዩ ከተማ ውስጥ በድብቅ ሲያመርት የነበረ ተቋም ተገኝቷል።

እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ንጽህና በጎደለው ቦታ የምግብ ዘይት በሱሉልታ ከተማ ውስጥ በድብቅ በማምረት በበርሜል በማሸግ ሲያከፋፍል የነበሩ የድርጅቶች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳሬክተር አቶ አበራ ደነቀ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የዘይት ምርቱ የት እንደተመረተ ፣ ከምን እንደ ተመረተና መቼ እንደተመረተ የሚገልጽ የገላጭ ጽሁፍ የሌለው ሲሆን ፤ንጽህናው ባልጠበቀ ቦታና በዛጉ አስራ ሁለት በርሜሎች ውስጥ የተከማቸ ዘይት መያዙ ተነግሯል፡፡

በተመሳሳይ በቡራዩ ከተማ በተደረገ ክትትል ባትባን የተባለ ስናክስ ሲያመርት የነበረው ድርጅት የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ብስኩቶች በመሰብሰብ እና ምንነታቸው ከማይታወቅ ማጣፈጫዎች ጋር ፈጭቶ እንደገና በስናክስ መልክ በማዘጋጀት ወደ ገበያ ለማቅረብ ሲያመርት በመገኘቱ እርምጃ እንደተወሰደበት አቶ አበራ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *