መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 23፤2014-በሱዳን መፈንቅለ መንግስት የፈጸሙት ሀይሎች እሁድ እለት ከእስር የፈቷቸዉን የኦማር አል በሽር ባልደረቦችን በድጋሚ አሰሩ ❗️

በሱዳን መፈንቅለ መንግስት የፈጸሙት ሀይሎች እሁድ እለት ከእስር የፈቷቸዉን የኦማር አል በሽር ባልደረቦችን በድጋሚ አሰሩ ❗️

የሱዳን መፈንቅለ መንግስት መሪዎች የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽርን አጋሮች እሁድ እለት ከእስር ቤት በማስፈታት የወቅቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግን ከስልጣናቸው አሰናብተዋል።ባለፈው ሳምንት በተደረገው መፈንቅለ መንግስት የቀድሞ መሪ እጅ እንዳለበት አልያም የኦማር አልበሽር ታማኝ ሀይሎች እንቅስቃሴ ስለመሆኑ ጠንካራው ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ከእስር ከተፈቱት መካከል የቀድሞው የገዢው ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ መሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኢብራሂም ጋንዶር ይገኙበታል።እነዚሁ ሰዎች ባለፈው አመት የሽግግር መንግስቱን ለማናጋት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወሳል፡፡መፈንቅለ መንግስቱን የፈጸመዉ ወታደራዊዉ ሀይል የደረሰበትክ ከፍተኛ ትችት ተከትሎ በድጋሚ ማሰሩ ተሰምቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሪነት የሽምግልና ጥረቶች በካርቱም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ቅዳሜ እና እሁድ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ፀረ መፈንቅለ መንግስት ሰልፎች ከተደረጉት በኋላ ሱቆች እና የንግድ እንቅስቃሴ ዝግ ሆነው ቀጥሏል፡፡

ባለሥልጣናቱ በኢንተርኔት እና በስልክ መስመሮች ላይ ገደብ መጣላቸዉን ተከትሎ ተቃዋሚዎች በራሪ ወረቀቶችን፣ የጽሑፍ መልእክት፣ የግጥም ጽሁፎችን እና በየመንደሩ ያሉ የተቃዉሞ ሰልፎችን በመጠቀም ጠንካራ ተቃዉሞ እንዲደረግ አስችለዋል፡፡ “እኛ የምናስተላልፈው መልእክት በወታደራዊ ሀይል አንገዛም ነው” ሲሉ የመብት ተሟጋች የሆኑት ታሃኒ አባስ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *