መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 23፤2014-በአዲስ አበባ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ 30 ተሸከርካሪዎች መሰረቃቸዉ ተነገረ❗️

በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው 2014 ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 30 ተሸከርካሪዎች መሰረቃቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ ከተሰረቁት 30 ተሸከርካሪዎች ውስጥ ከ20 በላይ የሚሆኑት የተሽከርካሪዎቹ እቃ ሳይጎድል ከአንድ ቦታ ተሰርቀው ሌላ አካባቢ መያዛቸውን ተገልጿል፡፡

የተሽከርካሪ ስርቆትን በተመለከተ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች እንደተፈጸሙ የተገጸ ሲሆን በአጠቃላይ ከፍተኛ የወንጀል ድርጊት የሚፈጸመው በቦሌ ሲሆን ዝቅተኛ ወንጀል ድርጊት የተፈጸመበት ደግሞ ልደታ መሆኑን ኮማንደሩ ገልጸዋል፡ አብዛኛው የስርቆት ወንጀል የተፈጸመው ተሸከርካሪዎች ጠባቂ በሌለባቸው አካባቢዎች ማቆም ፣የተሸከርካሪ ቁልፍ ውስጥ ጥለው በመሄድ እና የተሸከርካሪ መስታወትን ክፍት በማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ፖሊስ የመኪና ስርቆት በመፈፀም ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መሀል ለፍርድ በማቅረብ እንዲቀጡ ያደረገ ሲሆን በቀሪዎቹ ላይ ደግሞ ምርመራ የማጣራት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡በ2013 በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ 44 ተሸከርካሪዎች መሰረቃቸውን የሚታወስ ሲሆን ይህም ከተያዘው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ መቀነሱን ነው ኮማንደሩ ፋሲካ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *