መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 24፤2014-ጆ ባይደን በግላስጎው የአየር ንብረት ኮንፍራንስ ላይ የቻይናና ሩሲያ መሪዎች አለመገኘታቸውን ተቹ

ጆ ባይደን በግላስጎው የአየር ንብረት ኮንፍራንስ ላይ የቻይናና ሩሲያ መሪዎች አለመገኘታቸውን ተቹ

ትላንት ምሽት ጆ ባይደን ባደረጉት ንግግር የአየር ንብረት ለውጥ ግዙፍ ጉዳይ ቢሆ ቻይና እና ሩሲያ ይህንን ረግጠው ሄደዋል ብለዋል።እስከ ህዳር አጋማሽ በሚቆየው ጉባኤ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሆኑ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ አልተገኙም።

በካርቦን ልቀት ቻይና የአለማችን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን አሜሪካ ትከተላለች።ከአውሮጳ ህብረትና ህንድ በመቀጠል ሩሲያ አምስተኛዋ የካርቦን ልቀት ያለባት ሀገር ናት።በስኮትላንድ ግዙፍ ከተማ ግላስጎው ከ120 በላይ መሪዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤው ያልተገኙት ቻይናና ሩሲያ የደን ጭፍጨፋን ለመቀለበስ የተገባውን የቃልኪዳን ውል ፈርመዋል።ከባይደን ንግግር በፊት በቪዲዮ መልዕክት ያስተለፉት ፑቲን በደን አስተዳደር ላይ በተካሄደው ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ሩሲያ የደን መሬቶችን ለመጠበቅ ጠንካራ እርምጃዎችን ትወስዳለች” ሲሉ መናገራቸውን ከክሬምሊን የወጣው መግለጫ አመላክቷል።የፑቲን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በፑቲን ከጉባኤው መቅረት ዙሪያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *