መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 29፤2014-አሜሪካ ከ20 ወራቶች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት ድንበሯን ክፍት እንደምታደርግ አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ ለ20 ወራት ያህል የጣለችውን እገዳ በዛሬው እለት በማንሳት ሁለት ዙር የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለወሰዱ ሰዎች ድንበሯን እንደምትከፍት አስታውቃለች።ይህው እገዳ በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ በቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካይነት መጣሉ ይታወሳል።

ዩናይትድ ኪንግደም እና አውሮጳ ህብረት ጨምሮ ከ30 በላይ የአለም ሀገራት አሜሪካ በጣለችው እገዳ ክፉኛ ተጎድተዋል።በርካታ ቤተሰቦችን ለወራት የነጠለ ውሳኔ ሲሆን የቱሪዝም እንቅስቃሴው እንዲቋረጥ አስገድዷል።

እገዳው መነሳቱን ተከትሎ በአሜሪካ ሜክሲኮ ያሉ ከተሞች የንግድ እንቅስቃሴ ከወዲሁ የማንሰራራት ተስፋ አሳይቷል።የዩናይትድ አየር መንገድ በበኩሉ የመንገደኞች ብዛት 50 በመቶ ይጨምራል የሚል ግምት አስቀምጧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *