መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 29፤2014-ኢካዋስ በማሊ መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለ

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዋንኛ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥምረት ኢካዋስ የማሊ የሽግግር መንግስት በየካቲት ወር ፕሬዝዳንታዊ እና የህግ አውጪ ምክር ቤት አባላትን ምርጫ ለማካሄድ እንደማይችል ማሳወቁን ተከትሎ ማዕቀቡ ተጥሏል።እ..ኤ.አ በነሀሴ 2020 ማብቂያ ወታደራዊው ሀይል ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቡባከር ኬታን ከስልጣን ማስወገዱ ይታወሳል።

ከመፈንቅለ መንግስቱ በኃላ የማሊ ጊዜያዊ መንግስት በ18 ወራት ውስጥ ምርጫ እንደሚያደርግ ለምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ቃል ገብቶ ነበር።ሆኖም ግን በማሊ በቀጠለው የታጣቂ ቡድኖች ጥቃት የተነሳ እንደሚዘገይ ጊዜያዊ መንግስቱ አሳውቋል።

በሰሜናዊ ማሊ ከ2012 አንስቶ የታጠቁ አማፂ ቡድኖች የሚያደርሱት ጥቃት የ19 ሚሊዮን ህዝቦች መኖሪያ ለሆነችው ማሊ ብቻም ሳይሆን ለጎረቤት ሀገራቱ ቡርኪናፋሶና ኒጀር ስጋት ደቅኗል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *