መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 6፤2014-በሻሸመኔ ከተማ ከሸክላ አፈር እና ሳጋቱራ ተቀላቅሎ የቀረበ በርበሬ በቁጥጥር ስር ዋለ

በሻሸመኔ ከተማ ከሸክላ አፈር እና ሳጋቱራ ተቀላቅሎ የቀረበ በርበሬ በቁጥጥር ስር ዋለ

በሻሸመኔ ከተማ 01 ወረዳ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ የተዘጋጁ የምግብ ዘይት፣በርበሬ እና ስኳር እንዲሁም የአረም ማጥፊያ ኬሚካል በቁጥጥር ስር መዋሉን በሻሸመኔ ከተማ የወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ነጋ ጅማር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ የተመረቱት ህገወጥ ምርቶች የተያዙት በገበያ ላይ ለሸማቹ ለማቅረብ በነበረ ሂደት ላይ ስለመሆኑ ተገልፆል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ ባእድ ነገሮችን በመቀላቀል ለምግብነት የቀረበ 168 ሊትር ዘይት ፣ከሸክላ አፈር እና ሳጋቱራ ተቀላቅሎ የተመረተ 400 ኪሎ ግራም በርበሬ፣ ከተለያዩ የባእድ ነገሮች ጋር ተቀላቅሎ የተመረተ 430 ኪሎ ግራም ስኳር እንዲሁም 70 ሊትር የአገልግሎት ዘመኑ ያለፈበት የአረም መድሀኒት በቁጥጥር ስር ውሏል።

በሌላ በኩል በከተማው ወረዳ 01 እና 02 ውስጥ 345 ኪሎ ግራም የአደንዛዥ እፅ እና ከ700 በላይ የሺሻ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ነጋ ጅማር ጨምረዉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *