መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 6፤2014-የሞተ በሬ አርደው ለንግድ ያዋሉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ❗️

የሞተ በሬ አርደው ለንግድ ያዋሉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ❗️

በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ የፋሲል ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብደላ ነጋሽ ያደልቡት የነበረው ሰንጋ በሬ ይታመምባቸው እና ሲያሳክሙ ቆይተው በሬው ህይወቱ ያልፋል። ከዛም የሞተውን በሬ በተሽከርካሪ ጭነው በጎና ኬላ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ቆሻሻ ቦታ ላይ ይጥላሉ።

በሬውን ቆሻሻ ቦታ ጥለው ከሄዱደ በኃላ ደረጀ አበበ የተባለ ግለሰብ ከሶስት ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የሞተውን በሬ በማረድ በአካባቢው ለሚገኝ እቴነሽ ግርማ ለተባለ ምግብ ቤት ስጋውን ለምግብነት ያቀርባሉ። ሆኖም ግን የበሬው ባለቤት መረጃው በስልክ ተደውሎ ሲነገረው ወዲያውኑ ወደ ባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ በመደወል ጉዳዩን ያመለክታል።

ፖሊስ ጉዳዩን በጥልቀት ሲመረምር ቆይቶ የመጀመሪያ ተከሳሽ አቶ ደረጀ አበበ እንዲሁም ሁለተኛ ተከሳሽ የምግብ ቤቱ ስራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ሄኖክ ደመላሽን በቁጥጥር ስር ያውላል።

የባሌ ዞን አውሎ የጎባ ወረዳ ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ በዋለው ችሎት ሁለቱንም ተከሳሾች ጥፋተኛ ናቸው በማለት ተከሳሽ ደረጀ አበበን በአምስት አመት ጽኑ እስራት እንዲሁም ሄኖክ ደመላሽ ላይ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲሁም በሀምሳ ሁለት ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ ኮማንደር ምስር ዑመር በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *