መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 6፤2014-የጋዳፊ ወንድ ልጅ ለሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደር መሆኑ ተሰማ❗️

የሊቢያ የቀድሞ መሪ ሙአመር አል ጋዳፊ ልጅ በሚቀጥለው ወር በሀገሪቱ በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በእጩነት ተመዝግበዋል።ሰይፍ አል እስላም የአባታቸው የጋዳፊ አልጋወራሽ ተደርገው ይወሰዱ የነበረ ሲሆን ከ10 ዓመታት በፊት በህዝባዊ እምቢተኝነት ጋዳፊ በመወገዳቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ከ2011 አንስቶ ሊቢያ በግጭት እና የእርስ በእርስ ቀውስ እየተናጠች ትገኛለች።የመብት ተቆርቋሪ ቡድኖች በወርሃ ታህሳስ የሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ አይሆንም የሚል ስጋታቸውን እየገለፁ ይገኛል።

ሀያላን ሀገራትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ምርጫውን ለማደናቀፍ አልያም ውጤቱን ለማጭበርበር የሚሞክር ማንኛውም አካል ላይ ማዕቀብ እንደሚጠብቀው አስጠንቅቀዋል።በሊቢያ ባህላዊ ልብስ አሸብርቆ በእጩ ሰነድ ላይ የፈረመው የጋዳፊ ልጅ ፈጣሪ በእኛና በህዝባችን መካከል በእውነት ፍረድ ሲል ተናግሯል።

የሙአመር ጋዳፊን አረመኔያዊ የግፍ ግድያን ተከትሎ ሰይፍ አል ኢስላም በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር እንደነበር ይታወሳል።የሞት ፍርድ ተበይኖበት የነበረ ቢሆንም ከስድስት ዓመታት እስር በኃላ ተለቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *