መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 7፣2014-በጭሮ ከተማ የሰባት ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር የፈጸመዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ!

በጭሮ ከተማ የሰባት ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር የፈጸመዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ!

ተከሳሽ መሀመድ ኑሩ በጭሮ ከተማ ቀበሌ 02 ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከለሊቱ 10 ሰዓት የሰባት አመት ህጻን በማባበል አስገድዶ በመድፈር ወንጀል በእስራት ተቀጥቷል ።

ተከሳሽ ዘወትር ጫት ከሚቅምበት ቤት ደክሞኛል አረፍ ልበል በሚል ምክንያት የቤቱን ባለቤት የሆነችዉን ወ/ሮ ቀመሪያን በማስፈቀድ ወደ መኖሪያ ቤት የጓሮ ክፍል ከገባ በኋላ የወ/ሮ ቀመሪያ ሴት ልጅ የሆነችውን የሰባት አመት ህጻን በማባበል አስገድዶ ደፍሯል። ተከሳሹም ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው በፍጥነት ይሰወራል ።

ጉዳዩ የደረሰው ፖሊስም ባደረገው ክትትል ተከሳሹን በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ አቅርቧል ።

ጉዳዩን የተመለከተዉ የጭሮ ወረዳ ፍርድ ቤትም መዝገቡን መርምሮ በቀረበለት የሀኪም ማስረጃ እና የሰዉ ምስክር ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት በአስራ አምስት አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ሲሉ የጭሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሚካኤል ዳኜ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *