መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2014-ሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ትግራይ ከገቡ ከ1 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 872ቱን አሸባሪው ሕወሓት ለጦርነት እየተጠቀመባቸው ነዉ ተባለ

ሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ትግራይ ከገቡ ከ1 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 872ቱን አሸባሪው ሕወሓት ለጦርነት እየተጠቀመባቸው ነዉ ተባለ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬዉ እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫው መንግሥት በአሸባሪዉ ህወኃት ወረራ ለተቸገሩ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ትግራይ ከገቡ ከ1 ሺሕ 114 ተሽከርካሪዎች ውስጥ 872ቱን አሸባሪው ሕወሓት ለጦርነት እየተጠቀመባቸው ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ከበደ ዴሲሳ ተናግረዋል፡፡

የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪና ተራድኦ ድርጅቶች ለዜጎች እርዳታ ለማድረግ አንድ አካባቢ ሳይሆን በሁሉም ክፍሎች ትኩረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡ ያም ሆኖ መንግሥት በቻለው አቅም የሰብኣዊ እርዳታን እያደረሰ ቢሆንም እጥረት አለ ተብሎና ተጋኖ የሚወራው ሀሰት ነው ከአንድ ቦታ በስተቀር እየደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

አንዳንድ ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ለራሳቸው አላማ መንግሥትን ሲኮንኑና የአገሪቱን ስም እያጠፉ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ተቋማቱ የሽብር ቡድኑ ህወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚያደርሳቸውን ሰብዓዊ ጥሰቶች ለማንሳት እንደማይደፍሩም አንስተዋል፡፡

ይህም ወራሪውን ቡድን እየፈጸመ ያለውን ወንጀል ለመደበቅ ብሎም የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎት ለማሳካት የሚደርጉት ሴራ መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታዉ ከበደ ዴሲሳ በዛሬዉ መግለጫቸዉ ላይ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *