መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2014-በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት ያስቀጣል፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት ያስቀጣል፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ቀንአ ያዴታ (ዶ/ር) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት በማድረግ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

መመሪያው ሰላማዊ እና ፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመለየት፣ የሐሰት መታወቂያ የሚሰጡ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ለመለየት እንዲሁም የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ሆነው ያለ አግባብ ጊዜያዊ መታወቂያ የሚሰጡትን ለመቆጣጠር ያግዛል ብለዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ ከ3 እስከ 10 ዓመት ያስቀጣል ያሉት ኃላፊው ከህዳር 6 /2014 እስከ ህዳር 15/2014 በሚቆየው የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ሂደት ማህበረሰቡ መታወቂያ ማውጣት እንዳለበት ገልጸዋል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

የሎጂስቲክ እና የሰው ኃይል ቅድመ ዝግጅት ተካሂዶ አርብ ህዳር 10/2014 በየክፍለ ከተማው ጊዜያዊ መታወቂያ ለማህበረሰቡ ለመስጠት ዝግጅት መጀመሩም ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *