መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2014-በአዳማ ሀሰተኛ መታወቂያ በመያዝ ከሀገር ለውጣት ሲሞክሩ የተያዙ 10 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በአዳማ ሀሰተኛ መታወቂያ በመያዝ ከሀገር ለውጣት ሲሞክሩ የተያዙ 10 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በአዳማ ከተማ መስተዳድር ዳቤ ደንበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቦሩ ፋብሪካ ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ከአዲስ አበባ በመነሳት በመጓዝ ላይ እንዳሉ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡በቁጥር አስር እንደሆኑ የተገለጹት ወጣቶች በአንድ ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እንዳሉ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የያዙትን መታወቂያ በማሳየት ወደ ውጪ ሀገር ልንሄድ ነው በማለት ያሳዉቃሉ፡፡

ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር በማዋል መታወቂያቸውን አዉጥተናል ካሉበት ክፍለ ከተሞች ሲያጣራ ሀሰተኛ መታወቂያ መያዛቸውን እና ከየክፍለ ከተማው አለመመውጣቱን በማረጋገጥ ፖሊስ ማስረጃንውን በማጣራት የክስ መዝገቡን ለዞኑ አቃቤ ህግ ያቀርባል፡ የዞኑ አቃቤ ህግም ተከሳሾች በአቋራጭ በመበልጸግ እና ሀሰተኛ መታወቂያ በማውጣት ወንጀል ክስ በመመስረት ለአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀርባል፡፡

ፍርድ ቤቱም ተከሳሾች በፈፀሙት ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው በማለት እያንዳንዳቸውን በ4 ዓመት እስራት እና በ5 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል ሲሉ የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *