መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2014-በዩጋንዳ ለተፈጸመዉ ጥቃት አይኤስ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታወቀ

በዩጋንዳ ለተፈጸመዉ ጥቃት አይኤስ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታወቀ

አይኤስ እየተባለ የሚጠራው የሽብር ቡድን በትላንትናዉ እለት በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ከደረሰው ፍንዳታ ጀርባ እጁ እንዳለበት አስታዉቋል፡፡አይኤስ ቴሌግራም በተሰኘውን የማህበራዊ መልእክት መላኪያ መተግበሪያ በመጠቀም በፍንዳታዎቹ ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸዉ አስታዉቋል፡፡

በማክሰኞው ፍንዳታ ሶስት ንፁሀን ዜጎች እንዲሁም ሶስት አጥፍቶ ጠፊዎች መሞታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። በፍንዳታው ከ30 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።ፖሊስ አራተኛውን አጥፍቶ ጠፊ ነዉ ብሎ የጠረጠረውን ግለሰብ ተከታትሎ ተኩሶ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታዉቋል።

የአይኤስ የዜና ወኪል የሆነዉ አማቅ እንደዘገበዉ ዩጋንዳ በመካከለኛው አፍሪካ ከሚገኙ የአይኤስ ታጣቂዎች ጋር በሚደረገው ጦርነት ከሚሳተፉት ሀገራት መካከል አንዷ በመሆኗ የተነሳ በዚህ የጥቃት ኢላማ ዉስጥ ገብታለች፡፡አይ ኤስ በተያዘዉ ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ በዩጋንዳ ለተፈጸሙ ጥቃቶች ሃላፊነቱን ሲወስድ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ትላንትና ምሽት በተከታታይ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ጥቃቶቹን አውግዘዋል፡፡

ፖሊስ በትላንትናዉ እለት የተፈጸመውን ጥቃት የዩጋንዳ አማፅያን ቡድን መሰረቱን በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያደረገዉ ኤዲኤፍ መፈጸሙን አስታዉቆ ነበር፡፡ ኤዲኤፍ ከአይኤስ ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው ይናገራል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *