መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2014-የቡርኪናፋሶ ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ❗️

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ ኡጋዱጉ በትናንት እለት አደባባይ በመዉጣት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮክ ማርክ ካቦሬ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል።

ሰልፈኞቹ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ 28 ወታደሮችን እና አራት ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉትን በሰሜን እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ፕሬዚዳንቱን መቆጣጠር አልቻሉም ሲሉ ከሰዋል።

የደረሰዉን ጥቃት ተከትሎ በትላንትናዉ እለት የተጀመረው የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘን በዛሬዉ እለትም ቀጥሎ ዉሏ፤

በሰሜናዊ ማሊ ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኘው ሳምንታዊ ገበያ ሲሄዱ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት 12 ሰላማዊ ሰዎች ከሁለት ሳምንት በፊት መገደላቸዉ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *