በአሸባሪው የህውሃት ቡድን በተከፈተው ጥቃት የተነሳ አደጋ ላይ የወደቀውን የሀገርን ህልውና እንዲታደጉ ጥሪ የቀረበላቸው የቀድሞ ሰራዊት አባላት ጦሩን እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ተገልጿል ፡፡
ከእዚሁ ጥሪ ጋር በተያያዘ የቀድሞው የኢትዮጲያ ሰራዊት የድጋፍ እና ልማት 200 የሚሆኑ አባላቱ የህልውና ዘመቻውን ተቀላቅለው መሰረታዊ ስልጠና እየሰጡ እንደሚገኙ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ፡፡
ወደ ግንባር የሚያቀኑ ሰራዊት አባላት ከመኖራቸው እና ስልጠናውን የሚሰጡ የቀድሞው የጦር መሪዎች በስልጠና ተቋማት ከመገኘታቸው ባሻገር በአዲስ አበባ ከተማ አስተማማኝ የሆነ የደህንነት ስራ እንዲሰራ ከተቋማቱ ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ አስታውቀዋል ፡፡
ያለንበት ጊዜ ከፍተኛ ትኩረት እና መናበብ ፈጥሮ ሀገርን ከችግር መታደግ የሚያስፈልግበት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለእዚያ ይረዳ ዘንድ እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ፡፡
ናትናኤል ሀብታሙ !!