
ማስተገሻ በሚል ማንኛውም መድኃኒት ከመውሰድ ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ጥሪ ቀረበ❗️
በአለም ላይ ለሶስተኛ ጊዜ በኢትዮጲያ ደግሞ ለስድስተኛ ጊዜ ከህዳር 9እስከ 15 ግንዛቤን በመፍጠር የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መላመድን እንግታ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ ምክንያት በዓለም ላይ በየዓመቱ 700 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ።
በተጨማሪም በሰዎች፣በእንስሳት እንዲሁም በአካባቢዎ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን በ2025 በኢትዮጲያ ከስምንት እስከ ሃያ አራት ሚሊዮን ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። እንዲሁም አስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ስዎች ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችል ተጠቁሟል።
በሰዎች፣በእንስሳትና በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ተፅእኖ ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችል እቅድ በመንደፍ ለማህበረስቡ ግንዛቤን የማስጨበጥ ስራ እንደሚሰራ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
ማንኛውም ሰው ህመም ስለተሰማው ብቻ ማስታገሻ በሚል ማንኛውንም አይነት መድሃኒቶች መውሰድ እንደሌለበት ፤ህገወጥ የእንስሳት መድሃኒትንም ከመጠቀም ህብረተሰቡ እንዲቆጠብ ተጠይቋል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሃገራት ላይ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት እንደሚያደርስ ተገልጿል።
በአለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ በሰዎች ፣በአካባቢ እንዲሁም በእንስሳት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን የሚያስከትል ሲሆን ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንዲሁም ሌሎች ጉዳቶችንም ለመቆጣጠር ስትራቴጂዎች የተነደፉ ሲሆን የጤና ሚኒስትር ከሌሎች የግል እንዲሁም የመንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር እንዲሚሰራ እንዲሁም ከፍትኛ ትኩረት እንደሚሰጠው የጤና ሚንስትር ሚኒስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ