መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፣2014-በሱዳን ሀምዶክ ወደ ስልጣን ቢመለሱም አብዮቱን ሸጠዋል ተንኮል ነው ባሉ ደጋፊዎቻቸው ዘንድ ቁጣ ቀሰቀሰ ❗️

በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ በፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት የ16 ዓመቱ ታዳጊ ህይወቱ ማለፉን የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው አስታውቋል።ይህው ክስተት ያጋጠመው በትላንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከወታደራዊው መሪ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጋር የነበራቸውን ስምምነት ተከትሎ ነው።

ለሳምንታት የዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ሀምዶክ ከቡርሃን ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት ወደ ስልጣን ተመልሰዋል።የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት ቃል ገብተዋል።በስምምነቱ መሰረት ሀምዶክ እና አል ቡርሃን በ14 ጉዳዮች ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ሙሉ የሲቪል አገዛዝ እንዲኖር የሚፈልጉ የዲሞክራሲ ደጋፊ ቡድኖች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።በተቃውሞ ሂደት እንደ ጀግና ሲቆጠሩ የነበሩት ሀምዶክ በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ተንከለኛ ተቆጥረዋልስምምነቱ ከተገለፀ በኃላ ተቃዋሚዎች ሀምዶክ አብዮቱን ሸጠዋል ሲሉ ከሰዋል።

የሱዳን ፕሮፌሽናል ማህበር የተቃውሞውን ቡድን ከዳተኛ ሲል ገልጿል።በሀምዶክ ስምምነት የተበሳጩ ዜጎች በካርቱም፣ኦምዱርማን እና ባህሪ ከተሞች አደባባይ በመውጣት ቁጣቸውን ገልፀዋል።ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡት መካከል የ26 ዓመቱ ኦማር ኢብራሂም ሀምዶክ አበሳጭቶናል በማላ አማራጭ ስለሌለን በድጋሚ አደባባይ ወጥተናል ብለዋል።

አል ቡርሃን ስምምነቱ ሁሉን አቀፍ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።የቀድሞ ገዢ ፓርቲ ከሆነው ከብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ውጪ ማንንም ማግለል አንፈልግም ሲሉ ተደምጠዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *