
ብሊንከን የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ ወደ ስልጣን መመለሳቸውን የመጀመሪያ ደረጃ ነው ሲሉ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ አንቶኒ ብሊንከን የሱዳን መሪዎች የሀገሪቱን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ለመመለስ በፍጥነት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ወደ ቀድሞ ቦታቸው መመለስ እሁድ የተደረገዉን ስምምነት ተከትሎ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ለሱዳን እርዳታ ዋሽንግተን ከማድረጓ በፊት የበለጠ መሻሻል የሚኖርባቸዉ ጉዳዮች እንዳሉ አስታዉቀዋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ባካለፈው ወር የተካሄደዉን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት የሲቪል መሪዎች በሙሉ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡የሱዳን ገዢዉ የጦር አገዛዝ የሱዳን ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ኦማር አል ደጊርን እና የኡማ ፓርቲ አንዳንድ ፖለቲከኞችን ከእስር መልቀቁ ይታወሳል።
ከስልጣን የተባረረው የሽግግር መንግስት አባላት የእሁዱን ስምምነት ክህደት ሲሉ አጥብቀው ይተቻሉ፡፡
በስምኦን ደረጄ