መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፤2014-ነጋሽ ዋጌሾ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ል ርዕሰ መስተዳድር ሆነዉ ተሾሙ

ነጋሽ ዋጌሾ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ም/ል ርዕሰ መስተዳድር ሆነዉ ተሾሙ

አዲስ የተመሰረተው 11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ወንድሙ ኩርታን የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟል።በተጨማሪም ገነት መንገሻ ፎላን የክልሉ ምክር ቤቴ ምክትል አፈጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።

የክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖችና እና ከአንድ ልዩ ወረዳ የተወከሉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡፡፡በ11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የመስራች ጉባዔ ዶ/ር አንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን የክልሉ የርዕሰ መስተዳድ አድርጎ በአብላጫ ድምፅ ሾሟል።

በዚህም መሠረት ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው እንዲሠሩ በምክር ቤቱ 51 ድምፅና 1ታቅቦ ፀድቋል።ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በምክር ቤት ፊት ቀርበዉ ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *