መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፤2014-“ኢትዮጵያዊያን “ኢትዮጵያ” የሚለው የነፃነትና የአሸናፊነት ስም ከተቃጣበት አደጋ የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለበት” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

“ኢትዮጵያዊያን “ኢትዮጵያ” የሚለው የነፃነትና የአሸናፊነት ስም ከተቃጣበት አደጋ የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለበት” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ኢትዮጵያ የሚለውን የነፃነትና የአሸናፊነት ስም ከተቃጣበት አደጋ የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን ብለዋል፡፡ቤተ እምነቶች፣ አረጋዊያንና እናቶች በፀሎት፤ ጎልማሶች የአካቢያችሁን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅ፣ ወጣቶች ወደ ግምባር በመዝመት በዉስጥ ተላላኪ ባንዳዎች፣ በታሪካዊ ጠላቶቻችን እና በአንዳንድ ምዕራባውያን ሃገሮች ህብረት የተቃጣብንን እንደ አገር የመቆም የህልዉና አደጋ የትኛዉንም መስዋትነት በመክፈል እንቀልበልስ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

የቀደምቶቹን የጀግንነት እና የአልደፈርም ባይነት ታሪክ የሚያወራ ሳይሆን የራሱን ደማቅ ታሪክ በግምባር በጀግኖች መገኛ አዉድማ ሊፅፍ የተነሳ “ከአገሬ በፊት እኔን” ያስቀድመኝ ያለ መሪ ፈጣሪ አምላክ ሰጥቶናል። ኢትዮጵያን ቆርሶ ሊሸጣት ሳይሆን የወሰን አንድነቷን ሊያስከብር ፣ ሊደራደርባት ሳይሆን ሊደማላት፣ ሊገድላት ሳይሆን ሊሞትላት የተነሳ ጀግና መሪ ! ይህ ትዉልድ ኢትዮጵያን አጥንቷ እስኪቀር ግጠዉ የዘረፋትን፣ ትልቁ ታሪኳን አሳንሰው መዘባበቻ ያደረጓትን፣ በሰፈርና በጎጥ ከፋፍለው ያሳነሷትን የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎችን ‘ሆ !’ ብሎ ተነስቶ ከታንክና ከስናይፐር ጋር ተዋድቆ ወደ መጡበት የሸኘ ጀግና ትዉልድ ነዉ ብለዋል።

ዛሬ እነዛ በወጣቶቻችን ደም የታጠቡ፤ ፀረ ኢትዮጵያ አስተሳሰብ አራማጆች ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ህብረት ፈጥረው በብሩህ ተስፋ መንገድ ላይ እየተጓዘች ያለችውን ኢትዮጵያ በመበታተን ዳግም የቀድሞዉን የህወሓት የጨለማ ዘመን አገዛዝ ሊያሰፍኑ፣ ፍትህ ፊት ሊቆም ሲገባቸዉ ዳግም በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ የባርነት ቀንበር ለመጫን አሰፍስፈዋል ። “ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ በባንዳዎች እና ታሪካዊ ጠላቶች እጅ አትወድቅም !” ስንል “እኛ ተሰውተን እናድናታለን !” እያልን ነው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይህ ከሚሆን ሞቱን እንደሚመርጥ እርግጠኛ ነኝ። እኔም ይህን ከማይ ለሃገሬ መሰዋት ከብር እንደሆነ ላረጋግጥላቸሁ እወዳለሁ።ይህ የሚተኛበት ወቅት አይደለም፤ ንቁ ! ተነሱ ! ከፀረ ኢትዮጵያ አፍራሽ አስተሳሰብ አራማጆች እና ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ህብረት ፈጥረው ከተዋጉን ፊት እንቁም ! እንቅበራቸውም !

መላው የከማችን ነዋሪዎች ወጣቶች፣ ሴቶች አቅም ያለዉና የጤናዉ ሁኔታ የሚፈቅድለት በሙሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነዉን የዉድ መሪዉን የእናት አገር ጥሪ ተቀብሎ ዛሬውኑ በሁሉም ዘርፍ ውጊያውን ይቀላቀለዉ!! በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ደራሽ የሆናችሁ ትወልደ ኢትዮጵዊያን ዳያስፖራዎች ትግላችሁን፣ እምቢ ማለታችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉ ሲሉ ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *