መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፣2014-ሽመልስ ሃብቴ ትምህርት ቤት አካባቢ በፌስታል የተጣለ ቦንብ ተገኘ

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሽመልስ ሃብቴ ት/ት አካባቢ በፌስታል ተጥሎ የነበረ ሁለት ቦንብ እና አንድ የጦር ሜዳ መነፅር ከነማስቀመጫው በህብረሰቡ ጥቆማ ተጥሎ ምንም አይነት ጉዳት ሳያደርስ ተገኝቷል።

በተመሳሳይ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በህብረተሰቡ ጥቆማ የጦር መሳሪያና ልዩ ልዩ ወታደራዊ አልባሳት በቁጥጥር ስር ውለዋል። በወረዳ 10 አያት ዞን ሁለት መንገድ 14 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት በተደገረው ፍተሻና ብርበራ መሰረት 5 የእጅ ቦንብ ፣1 ክላሽን ኮቭ ጠብ መንጃ ከመሰል 190 ጥይቶች እና 5 ካርታ ጋር፣ 1 ሳንጃ ፣ የጥይት መከላከያ፣ የተለያዩ የመኪና ታርጋዎች ፣ የሞባይል ሲም ካርድ ፣የዝሆን ጥርስ ፣የሱዳን፣ የኤርትራ እና የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደንብ አልባሳት፣ልዩ ልዩ ሰነዶችና ማህተሞች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *